የእርቅነሽ ሰጋሮ ሶስተኛ ሰማይ መሄድ | የቢሾፕ ተክሌ እንደፈለገ ሰውን ከሞት ማንሳት ችሎታ | የእርቅነሽ በየቀኑ ማማለድ Ep 89

የእርቅነሽ ሰጋሮ ሶስተኛ ሰማይ መሄድ | የቢሾፕ ተክሌ እንደፈለገ ሰውን ከሞት ማንሳት ችሎታ | የእርቅነሽ በየቀኑ ማማለድ Ep 89

3,209 Просмотров

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤ/ክ የተጀመረው ከአሜሪካ በመጡ UPC ሚሽነሪዎች ነበር:: ቄስ ተክሌም UPC ትክክለኛ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ቤተክርስቲያን እንደሆነ እግዚአብሔር በራእይ ተገልጦላቸው እንደነገራቸው መስክረዋል:: ከዛም እምነቱን ተቀብለው ኢትዮጵያ ላለው ቤተክርስትያን ተወካይ ሆነው የተቀበሉትን የ “Oneness” UPC አስተምሮ ኢትዮጵያ ላይ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ ከአዋሳ በመጀመር መስበክ ጀመሩ:: ከ30 አመት በሗላ የኢትዮጵያ ቸርች ካደገች በሗላ ግን ኢየሱስ ከዳዊት ዘር በስጋ ምንም አልተካፈለም እርሱ ሰማያዊ ስጋ ይዞ ነው የመጣው በሚል ትምህርት ቄስ ተክሌ ማስተማር መጀመራቸው ከUPC ዶክትሪን ጋር ስለተጋጨ UPC ቄስ ተክሌን እና የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤ/ክ አውግዞ የስብከት ፈቃዳቸውንም በመሰረዝ ኢመፅሀፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ማስተማር መጀመራቸውን UPC በ2003 GC ይፋ አርጏል::

ከዛንም ቄስ ተክሌ ጭራሹን UPC ያልዳነ ቸርች መሆኑን ኢትዮጵያ ውስጥ ማስተማር ጀመሩ:: ኢየሱስ በስጋ በማርያም በኩል የዳዊትን ዘር ተካፍሏል የሚል ሰው ሁሉ የዘላለም ህይወት የለውም የሚል አደገኛ እና የተሳሳተ ትምህርት ማስተማር ጀመሩ::

በጣም የሚያሳዝነው ነገር ግን ለቄስ ተክሌ እግዚአብሔር በራእይ ተገልጦላቸው UPC ትክክለኛ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ቤተክርስቲያን እንደሆነ መሰከረልኝ ብለው ከአመታት በሗላ ደሞ UPC የተሳሳተ ቤተክርስቲያን ነው ብለው የራሳቸውን እንግዳ ትምህርት ማስተማር መጀራቸው ነው:: እግዚአብሔር ከጅምሩ ለኚ ሰው ተገልጦ ነግሯቸው ነበረ ወይስ የሀሰት እራይ ነበር ያዩት?

ኦንሊጂሰሶች ከተኛችሁበት ከባድ የሀይማኖት እንቅልፍ ንቁ እና እምነታችሁ ልክ መሆኑን እና አለመሆኑን በእግዚአብሔር ቃል ብርሀን መፈተሽ ጀምሩ:: እግዚአብሔር የመዳንን ብርሀን ያብራላችሁ!
Ссылки и html тэги не поддерживаются


Комментарии: